በአሜሪካ፣ካናዳ፣አውሮፓና አፍሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በአማራ ክልል የተፈጠረውን ቀውስና የፌዳራል መንግስቱ እየወሰደ ያልውን  ፍትሐዊ ያልሆን እርምጃ በማውገዝ ለተባበሩት መንግስታት የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ።
 
በአማራ ክልል መንግስት እየወሰደ ባለው ኢፍትሀዊ እርምጃ የተነሳ በየቦታው የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየተፈጸመ የሚለው ደብዳቤው የጅምላ አስር፣ ከፍርድ ውጪ የሆኑ ግድያዎችና የመሰረተ ልማት ውድመቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጿል።
ይህ ጭካኔ የተሞላው ድርጊት የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ የሚጻረርና በሀገራቸው እንደሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠሩ ያሉትን የአማራ ብሄር ተወላጆች ለክፋ አድጋ አጋልጧቸዋል።ስለዚህ የተባበሩት መንግስታት የአኢትዮጵያ መንግስት ጥቃቱን አንዲያቆም ግፊት ያድርግ፣ለዓመታት በዘለቀ ጦርነት ለተጎዳ ሕዝብ እርዳታ ይቅረብ፣መንግስት ረኃብን አንደጦር መሳሪያ መጠቀሙን ያቁም፣ ለሰላምና እርቅ መስፈን ሲባል የሰብአዊ መብት የፈጸሙት ተጠያቂ ይሁኑ ሲሉ አኢትዮጵያዊያኑ በደብዳቤ ጠይቀዋል።