የፋኖ ሕዝባዊ ኃይል በጎንደር ባደረገው ድንገተኛ ጥቃት ዋና የተባሉ የአድማ በታኝ ኃይል አዛዥ መገደላቸው ተሰማ።
 
ዛሬ መስከረም 28 በተፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት ከ16 በላይ የአድማ በታኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኢቪኤን ምንጮች ገልጸዋል። 
 
በደቡብ ጎንደር ልዩ ስሙ አመድ በር በሚባል አነስተኛ የገጠር ከተማ የፋኖ ታጋዮች በፈጸሙት አስደንጋጭ ጥቃት ከባህርዳር ወደ ደብረታቦር በተሽከርካሪ ሲጓዙ የነበሩ የአድማ በታኝ  ከፍተኛ አዛዦችና ከ16 በላይ አባላቱ መገደላቸው ታውቋል። ናዝሬት-አዳማ ላይ በብልጽግና ስልጠና ላይ የነበሩ ባለሥልጣናት በአድማ በታኝ ቡድኑ ታጅበው ሲመለስለሱ  እንደነበር ምንጮቹ ጠቁመዋል። 
የፌደራል መንግሥት ሐምሌ 28 ቀን2015ዓም በአማራ ክልል ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ጊዜ ጀምሮ ከ600 በላይ ንፁሐን ዐማሮች እንደተገደሉ ይገለጻል። 
የመከላከያ ሰራዊት በሚንቀሳቀስባቸውና እርምጃ በሚወስድባየው ቦታዎች ሁሉ የክልሉ አድማ በታኝና ደኅንነት ክንፎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ፋኖዎች በተደጋጋሚ በቁጣ ሲገልጹ ይደመጣል። 
በዚህ ምክንያት በየቦታው የሚያገለግሉ የብልጽግና አመራሮች ላይ ጥቃት እንደሚወስዱ ያስረዳሉ። ከወር በፊት የመሳሪያ ግምጃቤት አላስነካ ብለው እምቢተኛነት ያሳዩት የፋርጣ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አዲሱ ደብረታቦር ከተማ ላይ በፋኖ ሕዝባዊ ኃይል መገደላቸው ይታወሳል።