( Dejenmedia.com ) በኢትዮጵያ የአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎችና በመከላከያ ወታደሮች መካከል ግጭት እየሰፋ መምጣቱ ተዘገበ። ይህ በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት አብረው ከህወሃት ጋር ሲዋጉ የነበሩት የሁለቱ የቀድሞ አጋሮች ግንኙነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል።

ፋኖ ቀደም ሲል በትግራይ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የፌደራል ወታደሮችን የታደገ መሆኑ ሲታወቅ መደበኛ የእዝ መዋቅር የሌለው ከ አማራ ገበሬዎች የተውጣጣ ሚሊሻ ነው። ነገር ግን መንግስት የአማራን የጸጥታ ስጋት ችላ በማለት ትጥቅ ለማስፈታት በሚል የከፈተው ጥቃት ውጥረቱን በከፍተኛ ደረጃ እባብሶታል።

በቅርቡ የተከሰተው ግጭት በደብረታቦር አካባቢ ለሁለት ቀናት የተከሰተ ሲሆን የሆስፒታል ሀኪም ለደህንነት ሲባል ማንነታቸው ሳይገለጹ ለሮይተርስ እንደ ገለጹት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን 3 ግለሰቦች እና አስር ቀላል የአካል ጉዳት ጉዳት የደረሰባቸውን ተጎጂዎች ህክምና እግኝተዋል።

በደብረታቦር ከተማ ዳርቻዎች እየተካሄደ ያለው ውጊያ እና ወደ ከተማዋ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ በመቆየቱ ሁኔታውን ​​አሳሳቢ አድርጎታል። ከቆቦ ከተማ ወጣ ብሎም ውጊያ እንደነበር የተሰማ ቢሆንም ረቡዕ ግን ሁኔታው ​​መረጋጋቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ግጭቱ የጀመረው ከቀናት በፊት መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጭ አረጋግጧል። በግጭቱ ወቅት የፋኖ ታጣቂዎች የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ የሆነችውን የላሊበላ ከተማን እንደ ተቆጣተሩ የፋኖ ምንጮች ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ያለው የስፔን ኤምባሲ ጉዳዩን እየተባባሰ በመምጣቱ በላሊበላ የሚገኙ ስፔናውያን በሆቴሎች ወይም በመኖሪያ ቤታቸው እንዲቆዩ መክሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የመከላከያ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነን ጠቅሶ እንደዘገበው፥ የመከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ በፋኖ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የክልል ታጣዊዎችን የጸጥታ ኃይሎችን ወደ ፖሊስ ወይም ብሔራዊ ጦር ለማዋሃድ የሰጡትን ትእዛዝ ተከትሎ አንዳንድ ተቃዋሚዎች አማራን ለማዳከም የሚደረግ ሙከራ አድርገው ያዩታል። በተለይም ክልልሉ ከህወሃት የተደቀነበት የጽጥታ ስጋት ሳይቀረፍና በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ህወሃትን ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ጅላ ተብሉ የአማራ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ውሳኔ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞሞታል።