ከሶስት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ ታፍነው የተወሰዱት እስራኤላዊ-ኢትዮጵያዊው ፍራንሲስ አድባባይ፣ ሰኞ ከእገታ የተፈቱ ሲሆን ወደ እስራኤል በቅርቡም ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ታጋቹ ነጻ መውጣታቸውን ኤምባሲው ከአካባቢው የፖሊስ አዛዥ መረጃ እንደደረሰው አረጋግጧል።

እንደ ዘገባው፣ የ79 ዓመቱ አዛውንት አድባባይ፣ ከአጋቾቹ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኢትዮጵያ ልዩ ሃይሎች ነጻ መውጣታቸው አል ሞኒተር የተሰኘ የእስራ ኤል ሚድያ ዘግብዋል። 

ስለ ክስተቱ ብዙ ዝርዝሮች ግልጽ አይደሉም። ከታገቱ በኋላ ቤተሰቡ እንዲፈታ የገንዘብ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁኔታውን አውቆ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር ውይይት ማድርጉዋል።

የአፈና እና የማስፈቻ ገንዘብ ጥያቄው ትክክለኛ አይደለም የሚል ጥርጣሬዎች የነበረ ሲሆን ሚኒስቴሩ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር መስራቱን ቀጥሏል።

የአድባባይ ልጆች ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ እስራኤላዊው የፓርላማ አባል እርዳታ ጠይቀው ነበር። አድባባይን ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ከማውጣታቸው በፊት ታጋቾቹ በኢትዮጵያ ልዩ ሃይል አስቁሟቸዋል።