08-30-2023
በጋምቤላ ይኖሩ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ እንደሆነ የተባባሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ገለጸ።
በጁባ የሚገኙት የድረጅቱ ኮሚሽነር ፉሊፖ ግራንዲ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን በእርዳታ ምግብ ላይ በሚፈጽሙት ሙስና እንደሆነ በግልጽ ተናግረዋል።
በባልስልጣናቱ በሚፈጸመው ሙስና ምክንያት አሜሪካ የምትሰጠውን እርዳታ በማቆሟ የምግብ አጥረት በመፈጠሩ ስደተኞቹ ወደሀገራቸው እየተመለሱ መሆኑን ጠቁመዋል።
“ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን ችግሩን ለመቅረፍ አየተሞክረ ነው፡ ነገርግን ችግሩ የተፈጥረው በምግብ እርዳታ እቀባው ነው፡ ይኽ ለምን ያህል እንደሚዘልቅ አላውቅም” ብለዋል ኮሚሽነሩ ፊሊፖ ግራንዲ ፡
የተባባሩት መንግስታት በ2020 ባወጣው ሪፖርት መሰረት 342,765 የደቡብ ሱዳንብ ስደተኞች ጋምቤላ ውስጥ በሚገኙ ሰባት መጠላያ ጣቢያዎች ይኖራሉ።