በአለፈው ሐሙስ የአሜሪካ የመወሰኛ ምክር ቤት በርካታ አምባሳደሮችን ያካተተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እጩዎችን ቡድን ሹመት አጽድቋል። ከነዚህም መካከል በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው በይፋ የተሾሙት ኤርቪን ማሲንጋ አንዱ ናቸው።

በኢትዮጵያ የከፋ ሰብአዊ ሁኔታ እና በቀጠናው እየተከሰቱ ያሉ ፈተናዎች በገጠማት ወቅት ነው ማሲንጋ መሾማቸው ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑ ተገልጽዋል። ማሲንጋ በሕዝብ አገልግሎት ልምድ ያካበቱና እና በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ አግልግሎት ሰፊ ልምድ ያካበቱ ዲፕሎማት ናቸው።

ማሲንጋ በ1993 ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ ዋልሽ የውጭ አገልግሎት ትምህርት ቤት ባችለር ዲግሪ በኋላም በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ከኢቫንስ የህዝብ ፖሊሲ ​​እና አስተዳደር ትምህርት ቤት የህዝብ ፖሊሲ ​​ማስተር አግኝተዋል። ማሲንጋ በፓኪስታን፣ ሱዳን፣ ጊኒ፣ ዶሚኒካን ሪፑብሊክ፣ ቺሊ፣ አይቮሪ ኮስት እና ቻይናን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት በተለያዩ ስራዎች አገልግሏል። እንደ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ፣ የኢኮኖሚና የንግድ ጉዳዮች ቢሮ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ተወካይ ቢሮ እና የመረጃና ምርምር ቢሮ ባሉ የስራ ሃላፊነት ሰርተዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማሲንጋን እ.ኤ.አ. ጁላይ 27 ቀን 2023 ሴኔቱ ማሲንጋን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በማድረግ በእጩነት ማቅረባቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ውስብስብ የሆነ የሰብአዊ ቀውስ እና አህጉራዊ ፈተናዎች እየተጋረጡባት በመሆኗ ይህ ሹመት ለኢትዮጵያ ወሳኝ በሆነ ወቅት መጽደቁ ማሲንጋ በኢትዮጵያ ቆያታቸው ኢትዮጵያ ከከባችበት ቀውስና ትርምስ ለማውጣት የበኩላቸው አስተዋጾ እንደሚያበረክቱ ይታመናል።

አምባሳደር ማሲንጋ ባለፈው ግንቦት ወር በሴኔት በሰጡት ምስክርነት አገራቸውን ለማገልገል ለተሰጣቸው ዕድል ምስጋናቸውን ገልጸው ኢትዮጵያ ለዩናይትድ ስቴትስ ስትራቴጅካዊ አጋርነት ያላትን ጠቀሜታ በማጉላት በሁለትዮሽ ግንኙነቱ ውስጥ ያሉትን ተግዳሮቶች ጠቅሰዋል።

እ.ኤ.አ. በህዳር 2022 የሰላላም ስምምነት በህወሃትና በመንግስት መካከል እንዲደርስ ዩናይትድ ስቴትስ ያበረከትችውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አድንቀዋል። በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

ማሲንጋ በግጭቱ ወቅት ለተፈጸመው ግፍ የሽግግር ፍትህ እና ተጠያቂነት አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥቷል።

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጊ ማሲንጋን በትዊተር ላይ በመሾሙ እንኳን ደስ አለዎት በማለት ለቦታው የሚመጥን ሰው በመሾሙ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ በአምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን የሚመራ ሲሆን እ.ኤ.አ. ከአልፈው አመት የካቲት ወር ጀምሮ ቻርጄ ዴ እፌይርስ በመሆን አግልግለዋ።