የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አብነ ማቲዎስ

በበርካታ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያላት በአገሪቱ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ገጽታ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፋለች።

በአንድ ወቅት በአገሪቱ ፖለቲካ ትልቅ ተጽዕኖ የነበራት ቤተ ክርስቲያኒቱ በጊዜ ሂደት ይህ ሚናዋ እየደበዘዘ መጥቷል።

በአገሪቱ የሚከሰቱ የፖለቲካ ለውጦች የቤተ ክርስቲያኗን ሚና እየቀያየሩት ይገኛሉ።

ባለፉት ወራት ደግሞ በሁለት አቅጣጫ ፈተና ተደቅኖባት ነበር።

አንዱ ምላሽ ሲያገኝ ሁለተኛው መከፋፈልን አስከትሏል።

በፍሎሪዳ ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ እና ሃይማኖቶች ጥናት ክፍል ባልደረባ ለሆኑት ለፕሮፌሰር ቴሪ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አሁን ተፈጥሮ የታየው መከፋፈል ቀደም ብሎ አለመፈጠሩ “የሚደንቅ” ነው።

ለዚሀም ምክንያታቸው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላለፉት 30 ዓመታት በብሔር ፖለቲካ ሲናጥ መቆየቱ ነው።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cmj4v76zpe0o